Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

Dead Line: 2016-06-01

 

Tender Detail:

 





የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1. ቲሸርትና ኮፍያ ህትመት
  • ሎት 2. የቢሮ ቁሳቁስ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት 3. የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ

1. ተጫራቾች፡-

  • ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ
  • ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የተከፈለ መረጃ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ህንጻ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ 10ኛ ፎቅ የግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1. 10,000 /አስር ሺ ብር/ ለሎት 2. 5,000 /አምስት ሺ ብር/ ለሎት 3. 5,000.00 /አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ / CPO/ ማስያስ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ባሉት የስራ ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮው 50 ብር እየከፈሉ በመውሰድና ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ልክ በ3፡30 ሠዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት የቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እና የፋይናንሻል ዋጋ ኦሪጅናል እና ኮፒ ለብቻ በሌላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሳጥን እስከሚታሸግበት ቀን ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማስገበት አለባቸው፡፡

 

6. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0118494088

ስፖርት ኮሚሽን ህንጻ 10ኛ ፎቅ አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ