Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን

Dead Line: 2016-06-01

 

Tender Detail:

 






የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ጀነሬተር 500KVA፣ የሰራተኞች ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን፣ የብር መቁጠሪያ ማሽን እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-  

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

  2. በግዢ ኤጀንሲው ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ፣

  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በጨረታ ለመሳተፍ የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው፣

  4. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከባለስልጣን መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 304 መግዛት ይችላሉ፣

  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በትራንስፖርት ባለስልጣን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

  6. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚያቀርበው ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡

  7. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በ23/9/2008 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋና የቴክኒክ መግለጫ እና የዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፖዛል ሰነድ ዋናውንና ቅጂውን/ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣

  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115 51 02 44 የውስጥ መስመር 231 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን