Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የትምህርት ሚኒስቴር

Dead Line: 2016-06-07

 

Tender Detail:

 





ትምህርት ሚኒስቴር ቀጥሎ የተዘረዘሩት ዕቃዎችን


ተ.ቁ

የዕቃው መግለጫ

የጨረታው መለያ ቁጥር

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

የትምህርት ቤቶች ስፖርት ፕሮግራም አተገባበር መምሪያ

MoE/NCB/01/GoV-42/08

15,000.00

ግንቦት 29/08 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት

ግንቦት 29/08 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት

 

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ውድድር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡

  • በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት፣
  • በመ/ግ/ን/አ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11፡30 ሰዓት) ድረስ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል በመ/ቤታችን ግቢ አራት ኪሎ የሚገኘው አሮጌ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 101 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሌተር ኦፍ ከሬዲት ሊሆን ይችላል፡፡
  • መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

0111 56 55 58/30

የትምህርት ሚኒስቴር