Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የሀዋሳ ከተማ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ

Dead Line: 2016-06-06

 

Tender Detail:

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ግዥ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

 1. በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው፡-
 2. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡-
 3. በግብር ከፋይነት ተመዘግቦ ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
 4. የዘመኑን ግብር ግዴታውን የተወጣ መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል
 5. የጨረታ ሰነድ ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት በሀዋሳ ከተማ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) በመምሪያችን ስም የተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ /የተመሰከረ/ሲፒኦ / ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ዋናውንና ኮፒውን በመለየት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ይህ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ በወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 5-6 ሰዓት መምሪያችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገበያ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
 8. ጨረታው በ15ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባልተገኙበት ከሰዓት በኃላ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በመመሪያችን ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዓልና ሰንበት ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 9. የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለተሸነፈው ድርጅት ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
 10. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸለት ወዲያውኑ ወደ መምሪያችን መጥቶ የጨረታ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም ከ5 ቀናት በኃላ ቀደም ሲል ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
 11. መምሪያችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0462200665

የሀዋሳ ከተማ ፋ/ኢ/ል/መምሪያ