Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት
Dead Line: 2016-06-05
Tender Detail:
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በደብረብርሃን ከተማ ዋናው አስፋል መንገድ ላይ 7 ኪ/ሜ የመንገድ ላይ መብራት ዝርጋታ ለማሰራት በኤሌክትሮሜካኒካል (Electromechanical) ደረጃ 4 እና በላይ የሆኑ በዘርፉ የ2008 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይነት መለያ (TIN) ያላቸው ስራ ተቋራጮች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በመምጣት የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የስራውን ዝርዝር፣ ቴክኒካል መገምገሚያ መስፈርቶች እና የሚያስፈልጉ ሌሎች መረጃዎችን በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛሉ፡፡
- የቴክኒካል መወዳደሪያ ሰነዱ ኦሪጅናል እና ከሁለተ ኮፒ ጋር የድርጅቱ ህጋዊ ተወካይ ፊርማ እና ማህተም በየገጹ ተደርጎበት ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻው መቅረብ አለበት፡፡
- የፋይናንሻል መወዳደሪያ ሰነዱ ኦሪጅናል እና ከሁለት ኮፒ ጋር የድርጅቱ ህጋዊ ተወካይ ፊርማ እና ማህተም በየገጹ ተደርጎበት ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻው መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank guarantee) በስማቸው በጽ/ቤታችን አድራሻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማ ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ደጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በግልፅ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ22ኛው ቀን ሰኔ 3/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ዘግይቶ የቀረበ የመጫረቻ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የቴክኒካል ግምገማ ውጤት እና የፋይናንሻል ግምገማ የሚደረግበት /የሚከፈትበት/ ቀን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በአብክመ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት እና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስቁ 011 681 2857/2717 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመደወል መጠየቅ ይችላሉሉ፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የደብረበርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት