Tenders

 

Type: Building Materials

 

Organization: የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር

Dead Line: 2016-06-04

 

Tender Detail:

 





  1. የግብርና ሚኒስቴር ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ለዚህ ግዥ የሚሆን በጀት አለው፡፡


ተ.ቁ

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ቁጥር

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

1

ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና ግዢ 

16/2008

29/09/08 4፡00

29/09/08 4፡00

 

  1. መ/ቤቱ ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ግዥዎች የታሸገ የጨረታ ሰነድ እንዲያስረክቡ ወይም እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡
  2. ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ስነ ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ እና መመሪያ መሰረት ነው፡፡
  3. ፍላጎት ያለቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉትና ግብርና ሚ/ር የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩበት ከዚህ በታች በቁጥር 6ሀ በተገለጸው አድራሻ ነው፡፡
  4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ የተሟሉ የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከዚህ በታች በቁጥር 6ሀ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉሉ፡ የክፍያውም ዘዴ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ሰነዱ የሚላከው ክፍያው በመፈጸም የተጫራቹን ስም ለማስመዝገብና የጨረታ ሰነዱን ለመረከብ በሚቀርበው ተጫራቾች ወይም በተወካዩ አማካይነት ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ለሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት የለበትም፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6ሀ በተገለጸው አድራሻ ከላይ በተገለጸው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ወይም ከዚያ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሁሉም ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ጨረታው ተጫራች ወይም ወኪሎቻቸው /በጨረታው ለመገኘት የፈለጉ/ በተገኙበት በቁጥር 6ሀ በተገለጸው አድራሻ  ከላይ በተገለጸው የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡

      • ሀ)ሰነዱ የሚመረመርበት አድራሻ ኢ.ሲ.ኤም.ሲ መንገድ መገናኛ አለፍ ብሎ ከማዕድን ሚ/ር ጀርባ ግብርና ሚ/ር ሕንፃ ቁጥር  B 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-2 ስልክ ቁጥር 011 646 1242 ነው፡፡
      • ለ) ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት /የሚወስዱበት አድራሻ ከዚህ በላይ 6ሀ ላይ የተገለጸው ነው፡፡
      • ሐ) ጨረታ የሚላክበት አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 6ሀ የተገለጸው ነው፡፡
      • መ) ጨረታው የሚከትበት አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 6ሀ በተገለጸው አድራሻ ነው፡፡ 

  1. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ ምዕራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትን ሰነደች /ቅጾች/ በመሙላጽ ይሆናል፡፡

  2. ተጫራቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላት አለባቸው፡፡ ይህንን ያላሟላ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

    • ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ
    • ተጫራቹ የግብር ግዴታ መወጣቱን በማረጋገጥ በጨረታው ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ግብር ሰብሳቢ አካላት የተሰጠ ማስረጃ
    • ከብር 100,000 በላይ ዋጋ ባለው ዕቃ የሚወዳደሩ ከሆነ የተ.እ.ታክስ (VAT) ሰርተፊኬት
    • ተጫራቾች በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ደረገጽ /web site/ ለአቅራቢዎች ምዝገባ የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት ራሳቸውን ያስመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
    • የማጭበርብር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም ተደርጎበት መቅረብ ይኖርበታል፡፡

      1. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር /አዲስ አበባ