Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የዳሞቱ ፑላሳ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-04

 

Tender Detail:

 

 

 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለወረዳው ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት የሻንቶ ከተማ ውስጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የስራ ተቋራጭ

  1. በመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተመዝግበው የ2008 ዓ.ም ግብር በመክፈል ፈቃዳቸውን ያሳደሱና ተ.እ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቀድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ደረጃቸው  WC/WWC  7 እና ከዚያ በላይ በውሃ ስራዎች ግንባታ ፈቃድ ያላቸውና መልካም የስራ አፈፃፀም ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያለውን የሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዶክመንት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ በመክፈል ከዳሞት ፑላሳ ፋይ/ኢኮ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% /ሁለት ፐርሰንት/ ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና 2(ሁለት) የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገው ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በዳ/ፑ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት በነጠላ ዋጋ የማይነበቡና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0461191219 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

 

የዳሞቱ ፑላሳ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት