Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የልደታ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-03

 

Tender Detail:

 





የልደታ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎችን፣ የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ይጋዊ የንግድ ፈቃድ መታደሱን፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ፣ ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

  2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከአያት አደባባይ ወደ ጨፌ በሚወስደው መንገድ ወደ 10 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ ልደታ ቤቶች ግንባታ ፕ/ቅ/ጽ/ቤት ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 10ኛው (አስረኛው) ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

  3. ተጫራቾች 3000.00 (ሦስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ በልደታ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ (አስረኛው ቀን ቅዳሜ ዕለት ከሆነ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት) ድረስ ቦሌ አራብሳ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ውስጥ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያኑ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ቦሌ አራብሳ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  7. ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0910851375/0913762021 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የልደታ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት

ቅርንጫፍ ጽ/ቤት