Tenders

 

Type: Machinary

 

Organization: የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ባህር ዳር

Dead Line: 2016-06-09

 

Tender Detail:

 





የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክሮሜካኒካል እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ አቅራቢ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን በድረ ገፃችን አድራሻ WWW.awwce.com.et በነጻ ማግኘት ይችላል፡፡


No

Description of Goods

1

HDPE pipe welding machine different sizes

2

UPVC Pipe drilling machine

3

Submersible Pumps

4

Surface Pumps

5

Generators




በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር  (Tin No.) ያላቸው፡፡

  2. ተጫራቾች በድርጅታችን ስም የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላውን ዋጋውን 1.5% በሲ.ፒ.ኦ /በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  3. የሚያቀርቡትን ዋጋና ማስረጃዎች እንዲሁም ቴክኒካል ሰን በአንድ ላይ ኦሪጅናልና ኮፒ ለይቶ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 23 በአካል በመቅረብ ወይም በፈጣን የአየር መልዕክት በመላክ በታሸገው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በመቁጠር በ20ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ10፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

  5. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡

  6. ድርጅቱ ጨረታውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን 058 222 17 51 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻችን:-ባህር ዳር ቀበሌ 14 ከተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊዬም ፊት ለፊት ከአረጋዊያንና አርበኞች ህንፃ 3ኛ ፎቅ

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ባህር ዳር