Catagory Lists
Tenders
Type: Building Materials
Organization: የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
Dead Line: 2016-06-11
Tender Detail:
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን የተለያዩ ቧንቧዎች ድርጅታችን ድረስ በማቅረብ የሚሸጡ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ሎት 1 |
DCO pipe |
በቁጥር |
4,500 |
ሎት 2 |
GS pipe |
በቁጥር |
17,500 |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተ.እ.ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የተ.እ.ታክስን ጨምሮ ለሚያቀርቡት ዋጋ 1% (አንድ) ማስያዝ አለባቸው::
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን የእቃ መጠን እንዳስፈላጊነቱ እስከ 25% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለፁት ቧንቧዎች የሚያቀርቡበት ዋጋ እና ኦርጅናል ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን ከሚያሳይ ብሮሸር ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ለየብቻ ሆኖ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋናው መ/ቤት የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት አረጋውያን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለተገለፁት እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ከድርጅታችን ድረ ገጽ() ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 222 17 51 መደወል ይችላሉ፡፡
ፖ.ሣ.ቁ 106
ስልክ ቁጥር 058 220 45 27
Fax 058 226 60 11
ባህር ዳር
የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት