Catagory Lists
Tenders
Type: Construction
Organization: የደ/ወርቅ ከተማ መሪ ማ/ቤት
Dead Line: 2016-06-10
Tender Detail:
በአብክመ በመስራቅ ጎጃም ዞን በእና/እና/ወረዳ የደ/ወርቅ ከተማ መሪ ማ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በጥንቃቅን ለተደራጁ ሥራ አጥ ወጣቶች ለመስሪያ የሚሆን የሼድ ግንባታ ለማስገንባት ስለፈለግን ደረጃ GC/BC 10 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ የሥራ ተቋራጭ ለማጫረት ይፈልጋል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin) ያላቸው እና የወቅቱን የገበያ ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከ50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) በላይ ለሚገመቱ የጨረታ ሰነዶች የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦነድ/ ከጠቅላላ ዋጋ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው መዝጊያ በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተማቸውን እና ፊርማቸው የግንባታውን ኮፒ እና ኦርጅናሉን በማያያዝ በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግ ሰነዱን በማስገባት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 1 ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ለ21 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ22ኛው ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- በ22ኛው ቀን የበዓላተ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በ5 ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ የአሸነፈበትን የዕቃ ግንባታውን /የአገልግሎቱን/ ጠቅላላ ዋጋ 10 የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ /በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0586630004 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን በእና/እና ውጋ ወረዳ
የደ/ወርቅ ከተማ መሪ ማ/ቤት