Catagory Lists
Tenders
Type: Electronics
Organization: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት
Dead Line: 2016-06-18
Tender Detail:
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን ዋየር ቢዝነስ ታየር -1 ለተለያዩ የኦፕሬሽን እና ለአዳዲስ የመስመር መዘርጋት ስራዎች የሚያገለግሉ የጭነት መኪና፣ ደብል ጋቢና ፒካፕ እና ከሬኖችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
የሚፈለገው የተሽከርካሪ ብዛተ |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
ሎት 1 |
5 ቶን እና ከዚያ በላይ የመጫን/የመሸከም ጉልበት ያላቸው ተሽከርካሪዎች |
10 |
ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
ፒክ አፕ ደብል ጋቢና |
10 |
|||
ሎት 2 |
ከ6ቶን እና ከዚያ በላይ ክብደት ማንሳት የሚችሉ እና 12ሜ እና ከዛ በላይ ከፍታ ማንሳት የሚችሉ ክሬኖች |
3 |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ያከናወኑበትን እና የተሽከርካሪዎቹን የኢንሹራንስ ዋስትና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በድርጅቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዚህ በታች ከተጠቀሰው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
በኢተዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የም/ዕ/አ/ሪጅን ፕሮክዩርመንት ሎጄስቲክስና ዌርሃውሲንግ ቢሮ፡፡
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1233
የስልክ ቁጥር 011 557 29 34
ሜክሲኮ አደባባይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 አዲስ አበባ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢኤአ 002/2008 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓተ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በምዕ/አ/አ/ሪጅን ፕሮክዩርመንት ሎጄስቲክስና ዌርሃውሲንግ ቢሮ ቁጥር 08 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ብሄራዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት