Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

Dead Line: 2016-06-16

 

Tender Detail:

 





የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ፣ የቡና ጥራት ምርምር ማዕከል፣ የአጋርፋ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የገፈርሳ፣ አአምሮ ሕሙማን ማገገሚያ ማዕከል፣ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ የሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ የምግብ የመድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዮሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት  ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና መ/ቤት፣ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ስራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች፡-

  1. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሕንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 001 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. በጨረታ ሰነድ መመሪያ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ መሰረት የተሽከርካሪዎቹ ኮፈን ተከፍቶ ተጫራቾች እንዲያዩት ይደረጋል፡፡
  4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲሉ ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው በባለንብረት መስሪያ ቤቱ የሚሸፈን ሲሆን የሰም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎችን ግን በገዥው ይሸፈናል፡፡
  5. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ቢሮ ቁጥር 212 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በእርሳስ ተሞልቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  7. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው እንዲሁም አማራጭ ስልክ ቁጥር መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኙ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የእረፍት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  10. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ በማድረግ ሰነዱን በምን አግባብ አግኝቶ እንደተወዳደረ በሕግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
  11. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ በማድረግ ሰነዱን በምን አግባብ አግኝቶ እንደተወዳደረ በሕግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃልለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 154 04 25 ወይም 011 122 37 36 /08 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  14. አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት