Tenders

 

Type: Garment

 

Organization: ዘ ዲቨሎፕመንት ፈንድ

Dead Line: 2016-06-18

 

Tender Detail:

 





ዘ ዲቨሎፕመንት ፈንደ በመባል የሚታወቅ የኖርዌይ ዓለምአቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን፣ ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያየ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ጉርደ ሾላ አካባቢ በሚገኘው ዘ ዲቨሎፕመንት ፈንድ ቢሮ፣ ቲ.ኤስ.ቢጂ ሕንፃ (ቢሎስ ኬክ ቤት ያለበት ሕንፃ) 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ድረስ ሰነዱን በመግዛት መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 መቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ሲፒኦውን (CPO) በዘ ዲቨሎፕመን ፈንድ (The Development Fund) ስም ማሰራት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO)  ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘው ዘ ዲቨሎፕንት ፈንድ ቢሮ፣ ቲ.ኤስ.ቢጂ ሕንፃ (ቢሎስ ኬክ ቤት ያለበት) ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባ አለባቸው፡፡ የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ከዘ ዲቨሎፕመንት ፈንድ ቢሮ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 9፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘ ዲቨሎፕመንት ፈንድ ቢሮ ስብሰባ አዳራሻ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0116477254/55

ዘ ዲቨሎፕመንት ፈንድ