Tenders

 

Type: Machinary

 

Organization: በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-19

 

Tender Detail:

 




በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ መብራት አገልግሎት የሚሆን 30KVA/24kw ጀኔሬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች/አቅራቢዎች/ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፡፡
  3. ግብር የመክፈል  ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 2%  በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (C.P.O) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 05 መብራት ሀይል ጀርባ የቤቶች ልማት ህንፃ ላይ ከሚገኘው የባህር ዳር ገቢዎችና ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር R-304 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ 
  7. ተጫራቾ የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላትና በሚገባ በማሸግ እንዲሁም በዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የሐብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር R-304 ጠዋት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል /እሁድ/ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) C.P.O በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ /specificaiton/ በጨረታ ሰነዱ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ መረጃዎችን ኦርጅናል ለብቻው አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 2263346/05822633278/0913056614

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት