Tenders

 

Type: Cleaning Service

 

Organization: የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-19

 

Tender Detail:

 




የደ/ማ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለከተማ አስ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያና የጽዳት እቃዎችን ከአቅራቢ ድርጅቶች በሎት ጠቅላላ ዋጋ ድምር አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ፡-

  1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠን ብር 50,000.00 /ሀምሣ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)  ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ፣ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 20 /ሃያ ብር/ ብቻ በመክፈል ከገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 1%  በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በትሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግና ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ16ኛው ቀን ፍላጎት ባላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት እቃውን ደ/ማ/ከተማ አስ/ገን/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት/ን/ክፍል ይዞ በመምጣት ማስረከብ  አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 058 771 3362

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት