Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በጅማ ዞን በሊሙ ኮሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-06-18

 

Tender Detail:

 




በጅማ ዞን በሊሙ ኮሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2008 የበጀት ዘመን ባለ ሁለት ፎቅ ( 2) የሆነ አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ለማስገንባት ስለሚፈልግ በዚህ ዘርፍ ተሰማርታችሁ እየሰራችሁ ያላችሁትን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ እያሳወቅን መስፈርቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. ሕጋዊ ደረጃ አምስትና ከዚያ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ
  3. እስከ ዛሬ ለስራው ማንኛውም ሕንፃ በውሉ መሰረት ሰርቶ እና ጥራት ያለው ስራ መስራቱን ከአስሪው አካል ያገኘውን የምስጋና ወይም የድጋፍ ማስረጃ ያገኘውን ማቅረብ የሚችል
  4. ማንኛውም ተወዳዳሪ በመንግስት ግንባታ ውስጥ ለመወዳደር የተመዘገቡበትን ማስረጃና በማንኛውም የግንባታ ስራ ላይ ተሰማርቶ እያለ ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠ ስለመሆኑ
  5. የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኢ ወይም ኢንሹራንስ ተወዳድረው አጠቃላይ ዋጋ ለመወዳደር ካቀረበው ውስጥ 2 በባንክ ወይም በሕጋዊ ኢንሹራንስ ተቋም የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል
  6. ማንኛውም ተወዳዳሪ አንዱ በሌላኛው ላይ ተሞርክዞ ዋጋ ማቅረብ የለበትም ወይም በሌላኛው ተወዳዳሪ ዋጋ ላይ ተመርክዞ የራሱ ዋጋ ያቀረበ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ ከ28/9/2008 ዓ.ም እስከ 18/10/2008 ዓ.ም ከሊሙ ኮሣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአካል ወይም ሕጋዊ ወኪሉን ልኮ መግዛት ይችላል፡፡
  8. ተወዳዳሪው የገዛውን ሰነድ በትክክል ተረድቶ በተጠየቀው መሰረት ያለ ስርዝ ድልዝ በመሙላት ወይም በሚነበብ እጅ ጽሑፍ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
  9. ተወዳዳሪው በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልገባ ነገር ካለ  ከመሙላቱ በፊት ከታች በሚገለጸው መረጃ መሰረት በአካል ቀርቦ ወይም በስልክ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላል፡፡
  10. ማንኛውም ተወዳዳሪ በአቋራጭ ጨረታውን አሸናፊ ለመሆን ያልተገባ እንቅስቃሴ  ካደረገ በጨረታ ህግ መሰረት ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ፈሶ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ ባዘጋጀው ግንባታ ማሰሪያ ቦታ አዋሳኝ ክልሎችንና የሕንፃ ግንባታ ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ ለመስራት ሙሉ አቅም ያለውና ዝግጁ የሆነ
  12. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ከ28/09/2009 ዓ.ም እስከ 18/10/2008 ዓ.ም በማንኛውም የስራ ሰዓት ይሆናል፡፡ 
  13. ጨረታው በ18/10/2008 ዓ.ም በ6፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  14. በጨረታው አከ,ፋፈት ስነ ስርዓት ላይ ፍላጎት ያለው ማንኛውም መገኘት ይችላል፡፡
  15. በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው አሸናፊው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አምስት የስራ ቀናት ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
  16. ከ1ኛ ተራ ቁጥር እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር በዋጋ በደረጃ ከተቀመጡት ውጭ የሌሎች ተወዳዳሪዎች ሲፒኦ በ5 ቀን ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
  17. ከ1ኛ ተራ ቁጥር እስከ 3ኛ ድረስ ካሉት ተወዳዳሪዎች በ1ኛ ደረጃ የተቀመጠ ቀርቦ የውል ስምምነት ሲፈጸም ለቀሩት 2ኛና 3ኛ ደረጃ ሲፒኦ ይመለሳል፡፡
  18. ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው ላይ በአካል መገኘት ያለበት ሲሆን መገኘት ካልቻለ በሕጋዊ የፍ/ቤት ውክልና የጸደቀ ተወካይ ማቅረብ ይችላል፡፡
  19. የጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከታወቀበት ቀን ከአምስት ቀናት በኃላ ባሉት ተከታታይ ሁለት ቀናት ውስጥ በአካል ቀርቦ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ 10 (አስር ፐርሰንት) በሲፒኦ ወይም ኢንሹራንስ (በባንክ ወይም ከሕጋዊ ኢንሹራንስ) ተቋም የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  20. የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መስሪያ ቤቱ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- የሊሙ ኮሣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር

0472240062/0917829905/0912802529/0932472678/0917018013

በአ/ብ/ክ/መ በጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት