Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የዲታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-07-02

 

Tender Detail:

 



የዲታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2008 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ፈረስ ጉልበት ያላቸውንና የተለያየ አገር ምርት ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፣

  1. በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ በሰነዱ ላይ መግለጽ የሚችል፣
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
  4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
  5. ከላይ የተዘረዘሩትን ምርቶችን መ/ቤቱ ወዳለበት ወደ ዲታ ወረዳ ማዕከል ማድረስ የሚችል፣
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ወደ መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛትና ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፣
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ በጨረታው ያሸነፈበትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ አቅርቦ እስከ ሚጨርስበት ቀን ነው፣
  9. የጨረታ ሰነዱ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ተሸጦ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ባይሆን የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ቀኑ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ ይሆናል፣
  10. የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፣
  11. አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዕቃ ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መግለጽ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ቀን፣ ስምና ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም ማስፈር አለባቸው፣
  12. የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል ጽሁፍ ልዩነት ቢኖር የነጠላው እና የጠቅላላ ዋጋ የፊደል መግለጫዎች ቀጥታ ይወስዳሉ፣
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫት ማካተቱን ወይም አለማካተቱን ካልገለጹ የቀረበው ዋጋ ቫት አጠቃሎ እንደቀረበ ተደርጎ ይወሰዳል፣
  14. አሸናፊው አቅራቢ የሚለየው ለተጠየቁት ጠቅላላ ዕቃዎች ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢው ይሆናል፣
  15. ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኃላ የቀረበ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
  16. የገበያ ዋጋ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀናት ብቻ ነው፣

አድራሻ፡- የጋሞ ጎፋ ዞን ማዕከል ከሆናቸው አርባ ምንጭ 58 ኪ.ሜ ርቀት ላይ፣ ከጨንቻ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንገኛለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 0916 85 32 89/ 0910 92 83 51/ 09 10 56 24 38/ 09 28 83 13 84 ይደውሉ፡፡                     በጋሞ ጎፋ ዞን ደታ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት