Tenders

 

Type: Electronics

 

Organization: የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ

Dead Line: 2016-07-02

 

Tender Detail:

 




የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ለሃዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የአቅጣጫ ጠቀሚ ዘመናዊ መብራቶች(Street Adress Sign) ስራ ለማካሄድ በመስኩ የተሰማሩ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን  መወዳደር ይችላሉ

  1. በኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ዘርፍ  የተሰማሩ ደረጃ 2/ሁለት/እና ከዚህ በላይ ያላቸው
  2. በስራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተቋራጭነት ብቃት  ማረጋገጫ ማስክር  ወረቀት የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT)ተመዝጋቢ የሆነ
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1% ከባንክ ሲፒኦ/ባንክ ጋራንት/ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  5. የጨረታ ሰነዱ ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር  3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲሰ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/ ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡
  6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው  በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ/ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል/በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 2፡30-6፡00 ሰዓት በፋይ/ኢኮ/ልማት መማሪያ ቢሮ ቁጥር  6 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም  ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚገባበትን የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው  ስራ ቀን ይከፈታል የጨረታው ቴክኒካል ግምገማ በጨረታ ሰነዱ በዝርዝር በተቀመጡ የቴክኒካል ብቃት ግምገማ መስፈርት መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡ ቴክኒካል ግምገማ ያለፈ ድርጅት ብቻ ለፋይናንሻል ይጋበዛሉ፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ  አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462209963/0462200665

ፋክስ ቁጥር 0462208532 ፖ.ስ.ቁጥር 02

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ