Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የንግድ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Dead Line: 2016-02-14

 

Tender Detail:

 

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የንግድ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በዳውሮ ዞን በዋካ ከተማ አስተዳደር በቱላ ክ/ከተማ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላትን ከዚህ በታች የተዘረተሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ማስገባት ይፈልጋል፡፡በዚህም መሰረት፡-

    1. ደረጃቸው GC-7/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ

    2. ፍቃዳቸውንና የከተማ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ ሠርተፊኬታቸውን ለ2008 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡

    3. ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘውትር በሥራ ቀናት የንግድ ኢንዲስትሪ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

    4. ተጫራቸች የጨረታ ዋስትና 50,000(ሃምሳ ሺ ብር) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

    5. ተጫራቾች ጨረታው ሰነዳቸውን የቴክኒክና ፋይናንሻል አንድ አነድ ኦርጅናልና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻቸው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግና ጠቅላላውን በአንድ ሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ቢሮ ለዚሁ ባዘሃጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት አለባችሁ፡፡

    6. 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

    7. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት መ/ቤቱ የግ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በመክተት ይታሸግና በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

    8. 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከናወን ይሆናል፡፡

    9. መ/ቤቱ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

        ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-046 220 39 61/046 220 65 82 ይደውሉ፡፡