Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

Dead Line: 2016-07-09

 

Tender Detail:

 




የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በ2009 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ማለትም አጀንዳዎች፣ ፖስታ ካርድ፣ የጠረጴዛ ካላንደር፣ የግድግዳ ካላንደሮችና የኪስ ካላንደር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-

 

ሎት

የጨረታ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን

001

አጀንዳ

ፖስታ ካርድ

የጠረጴዛ ካላንደር

የግድግዳ ካላንደር

የኪስ ካላንደር

10,000

00

 

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል በፅሁፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  5. የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ኪሊራንስ ማቅረብ አለበት፡፡
  8. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ህትመቶች በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
  13. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች እቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
  14. በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶች ተገምግመው አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን የህትመት ውጤቶች ሙሉ ለሙሉ አዘጋጅቶ ገቢ ከማድረጉ በፊት ከየህትመት ዓይነቱ ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
  15. ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢና ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  16. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  17. በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፡፡
  18. የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡
  19. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  20. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 111 04 48

                          011 126 43 61 የውስጥ ስልክ 1209/1332

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን