Tenders

 

Type: Agricultural Products

 

Organization: የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር

Dead Line: 2016-07-27

 

Tender Detail:

 

 

  1. የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ከዚህ በታች የተገለጽትን ህትመቶች በጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ለዚህ ግዥ የሚሆን በጀት ነው፡፡

 

ተ.ቁ

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ቁጥር

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት

 የሚከፈትበት ቀንና እና ሰዓት

1

የአጀንዳ ህትመት የካላደር ህትመት ፖስታ ካርድ ህትመት

20/2008

19/11/08 4፡00 ሰዓት

19/11/08  4፡30  ሰዓት

 

መ/ቤቱ ብቁ ተጫራቾች ለሚወዳደራቸው ህትመቶች ግዥ የታሸገ የጨረታ ሰነድ እንዲያስረክብ ወይም እንዲያቆይ ይጋበዛል፡፡

  1. ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዩጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ  መንግሥት በወጣው የመንግሥት የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት ነው፡፡
  2. ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚ/ር የጨረታ ሰነዶች የሚመረመሩበት ከዚህ በታች በቁጥር 6 በተገለጸው አድራሻ ነው፡፡
  3. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በአማራኛ ቋንቋ  የተዘጋጃ የተሟሉ የጨረታ ሰነዶችን ለእንዳንዱ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዚህ በታች በቁጥር  6 በተገለጻው  አድራሻ ማግኘት ይችላል፡፡ የክፍያውም ግንዘብ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ሰነዱ የሚላከው ክፍያ በመፈጸም የተጫራቹን ስም ለማስመዝገብና የጨረታ ሰነዱን ለመረከብ ወይም በተወካዩ አማካይነት ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ለሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት የለበትም፡፡
  4. ተጫረቾች የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6 በተገለጸን አድራሻ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ወይም በፊት በማቅረብ አለባቸው፡፡ ሁሉም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00 (ሦስት ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ዋስትና ያቀወባሉ፡፡ ዘግይቶ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይፈልጋል፡፡ ጨረታው የተጫራቾች ወኪሎች (በጨረታ ለመገኘት የፈለጉ) በተገኙበት በቁጥር 6 በተገለጸው አድራሻ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ሀ/ሰነዱ የሚመረመርበት አድራሻ ጉርድ ሾላ የኢትዩጵያ ግብርና ምርምር  አጠገብ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚነስቴር የግዥ ኬዝቲም 1ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 011 6 46 12 42 ነው፡፡

ለ/ ሰነዱ ወጪ የሚሆንበት /\ሚወሰድበት እድራሻ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ግዥ ኬዝ ቲም 1ኛ ፎቅ

ሐ/ ጨረታ የሚላክበት አድራሻ ግዥ ኬዝ ቲም 1ኛ ፎቅ

መ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው አድራሻ ነው፡፡

  1. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ ምዕራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትን ሰነዶች (ቅጾች) በመሙላት ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚከተሉት ሰነዶች/ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህንን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

        •  i.    ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ
        •  ii.   የግብር ግዴታ መውጣቱን በመግለጽ በዚሁ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችል መሆኑን የሚገልጽ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ
        • iii.    ከብር 100000 በላይ ዋጋ ባለው ዕቃ የሚወዳደሩ ከሆነ የተ.እ.ታክስ (VAT) ሰርፍፊኬት
        • iv.    የግንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም በመንግሥት ግዠ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ፎርም ላይ የተመዘገበ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ 
        • v.    የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቾች ድርጅት ፈርማና ማህተም የተደረገበት፡፡

  1. መ/ቤቱ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡