Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: መቱ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2016-07-30

 

Tender Detail:

 

 


 መቱ ዩኒቨርሲቲ በ2009 ዓ.ም የበጀት ዘመን ለተማሪዎች ቀለብ የሚውል የተለያዩ የምግብ ግብአቶችን ለዋና ግቢና ካምፖስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

የጨረታው መስፈርት

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

  2. የታክስ መለያ ቁጥር () ያላቸው፣

  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ማስረጃ ሰርተፍኬት ያላቸው፣

  4. በዘርፉ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማስረጃ ያላቸው፣

  5. ከግብር ነፃ መሆናቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች ባለስልጣን ማስረጃ የሚያቀርቡ፤

  6. የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ማስያዝ የሚችሉ፣

  7. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው 10% በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ፣

  8. ተጫራቾች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስተው ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት መቱ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ቢሮ ቁጥር 108 የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 400 ብር በመግዛት ከሰነዱ ጋር በሚሰጥ ቅጽ ላይ ብቻ ዋጋቸው ሞልተው በመፈረምና ሕጋዊ ማህተም በማድረግ በመጨረሻው ዕለት 23/11/2008 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ሰነዱን መቱ ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀንና ቦታ በ4፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡

  9. የዳቦና የሥጋ አቅርቦት በተመለከተ ተወዳዳሪዎች ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ለትላልቅ ድርጅት ማቅረባቸውን የሚገልጽ የመልካም የስራ አፈጻጸም የድጋፍ ደብዳቤ ማስረጃ ከድርጅቱ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም በቂ የማዘጋጃ ቦታና በቂ የሰው ኃይል ሊኖራቸው ይገባል፤

10. ሕጋዊ ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የምግብ ግብዓቶች ላይ ለማሳያነት የሚያገለግሉ ናሙና ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ይዘው መቅረብ የዕቃው መረካከቢያ ቦታ መቱ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢና በደሌ ካምፓስ ግቢ መጋዘን ነው፡፡

11. ማስጫና ማስወረድ የትራንስፖርት ወጪዎች የሻጭ ግዴታ ናቸው፤

12. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤

13. የምግብ ጥሬ ግብዓቶች ብዛት ሊጨምር ሊቀንስ ይችላል፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ፡- 251471410511 , 251925947532