Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: መቱ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2016-07-30

 

Tender Detail:

 

 


መቱ ዩኒቨርሲቲ
በ2009 ዓ.ም የበጀት ዘመን የተለያዩ ንብረቶችን ከተለያየ ቦታ ለማመላለስ ወይም ለማጓጓዝ የጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

የጨረታው መስፈርት

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የታክስ መለያ ቁጥር () የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡

  2. የጨረታ ማስከበሪያ 80,000 /ሰማንያ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ማስያዝ የሚችሉ፡፡

  3. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ማስያዝ የሚችሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የባለቤትነት ሊብሬና የ2008 ዓ.መ ቦሎ ያሳደሱበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

  5. ተወዳዳሪዎች የታደሰ የመድን ሽፋን ዋስትና አለባቸው፡፡

  6. ለዩኒቨርሲቲው በጫነው ዕቃ ላይ ምንም ዓይነት የሌላ ወገን ዕቃ መጫን አይፈቀድም፡፡

  7. የጫነውን ንብረት በሙሉ ቆጥሮ በመረከብ ቆጥሮ ማስረከብ የሚችል፡፡

  8. ዕቃውን ከታዘዘበት ቦታ የማስጫንና ማውረጃ ወጪዎች የተጫራች ግዴታ ነው

  9. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስተው ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት መቱ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ቢሮ ቁጥር 108 የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 200 ብር በመግዛት ከሰነዱ ጋር በሚሰጥ ቅጽ ላይ ብቻ ዋጋቸውን ሞልተው በመፈረምና ሕጋዊ ማህተም በማድረግ በመጨረሻው ዕለት ሀሙስ 23/11/2008 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ሰነዱን መቱ ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀንና ቦታ በ4፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡

10. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

11. የጭነት አገልግሎቱ ብዛት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ፡- 251471410511