Catagory Lists
Tenders
Type: Multiple Items
Organization: የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት
Dead Line: 2016-08-20
Tender Detail:
የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለሚገኙት ለህግ ታራሚዎች ጥሬ የምግብ እህልና የበሰለ ምግብ የተለያዩ ማጣፈጫዎችን አንዲሁም የማገዶ እንጨት ከነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 (አምስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀምና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ማንኛውም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የ2008 ዓ.ም የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አቅራቢዎች የዞኑ ማረሚያ ቤት በሚገኝበት ከተማ (አሰላ ከተማ) ውስጥ ለምግብ እህል ከምችት የሚያገለግሉ መጋዘን ያላቸው ወይም የበሰሉ ምግቦችን ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 (ሰላሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በዞኑ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት የግዢ ዕቅድና አስተ/ፋይናንስ ድጋፍ ሰጪ የስራ ሂደት ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በዝግ ፖስታ በማድረግ በአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያን ከመቶ ሁለት (2 ፐርሰንት) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ብቻ እና የእህሉን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የሚቀርቡ ማህበራት ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሐምሌ 20 ቀን 2008 ዓ.ም ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ በ5፡00 ሰዓት አርሲ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎችና የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ውሉን የመሰረዝም ሆነ ሙሉ በሙሉ የማቋረጭ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የምግብ እህሉንም ሆነ ማጣፈጫዎችን እና የማገዶ እንጨት በራሳቸው መጓጓዣ ወጭ እስከ ማረሚያ ቤት ድረስ ማቅረብ ወይም የበሰለ ምግብ ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- 10. ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 022331040/0922651585 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡