Catagory Lists
Tenders
Type: Machinary
Organization: አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
Dead Line: 2016-08-03
Tender Detail:
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የጥገና ሥራዎች በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ለሁለት ዓመት በኮንትራት (ከ2009 ዓ.ም እስከ 2010 በጀት ዓመት) ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የ2008 ዓ.ም ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 09 ቂሊንጦ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ከፍ ብሎ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ ሕንፃ ቁጥር 24 ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በተመሳሳይ አጠቃላይ የጥገና ስራዎች በጥንቃቅንና አነስተኛ የተደራጁና የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ይወዳደራሉ፡፡
- ጨረታው ባለአንድ ፖስታ ሲሆን የተጠየቀውን የብቃት መስፈርት ያሟላ በዋጋ ይወዳደራል፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ሐምሌ 26 ቀን 2008 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በሲፒኦ () ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቂሊንጦ ቀበሌ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 3 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ከአዲስ አበባ ከተማ በቃሊቲ መስመር መንገድ ወይም በጎሮ መስመር በአዲሱ ቱሉ ዲምቱ ደ/ዘይት መንገድ በቀላሉ መድረስ ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0118 69 60 94 /0118 69 61 20