Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተር ፕራይዝ

Dead Line: 2016-08-15

 

Tender Detail:

 



የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተር ፕራይዝ ለደብረዘይት ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል supply, insall, test and commission audio system ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡ ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት፡፡

  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋናው መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ፣ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (Quality certificate) በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡

  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ጨረታው ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

  8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114 40 34 33/34

ማዞሪያ 0114 42 22 70/71/72

ፖ.ሳ.ቁ 3414

ፋክስ፡- 0114 40 04 71/0114 42 07 46