Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት

Dead Line: 2016-08-27

 

Tender Detail:

 



የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የተለያዩ የመኪና ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ፍላጊትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊና የታደሰ ወይም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውንና የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የተመዘገቡ መሆኑን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. የጨረታው ሰነድ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 27/12/2008 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ዘወትር በስራ ቀናትና ቅዳሜ 2፡30 እስከ 6፡30 አዲስ አበባ ቦሌ ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20/የድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም አዳማ ከሚገኘው የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 92 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል መግዛተ ይችላሉ፡፡

  3. የጨረታው ሰነድ በሁለት /አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ/ በሰም በማሸግ እስከ 27/12/2008 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ቦሌ ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20/የድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኙብ ጨረታው በተዘጋበት እለት 27/12/2008 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አዲስ አበባ ቦሌ ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡

  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋው 1% /አንድ ፐርሰንት/ በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  6. ከሚፈለጉት ጎማዎች መካከል ለከፊሎቹ ብቻ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት ላያስገኝ ይችላል፡፡

  7. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በውሉ መሠረት ዕቃዎቹን አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር 022 112 21 73 /022 110 08 57 /022 111 03 07 ደውለው ይጠይቁ፡፡

የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አዳማ