Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2016-08-22

 

Tender Detail:

 

 

 

 በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት የሚውል፡-

ሎት 1፡- የጤና ሳይንስና የግብርና የላብ ፈርኒቸር ስራዎች ከነገጠማው እና የሌክቸር ሆል ወንበር ሰርቶ መግጠም፡፡

ሎተ 2፡- ለተለያዩ ግንባታ የሚያገለግሉ ግብዓቶች እና የማገዶ እንጨት፡፡ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/መስራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነጻ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉና ሌሎች ዶክሜንቶች ካሉ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ አዲስ አበባ ቢሮ በመቅረብ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ጨረታውን በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡ 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ለሎተ 2፡- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 3፡- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በ90 ቀን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እንዲሁም አንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ አለፍ ብሎ በሚገኘው ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ በማቅረብ ጨረታው ከወጣ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጠዋት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  5. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 የቴክኒካል ዶክሜንት የሚከፈት አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ አዲስ አበባ ሲሆን የህጋዊ ዶክሜንቶችና ቴክኒካል ምዘናውን ያለፉ ተወዳዳሪዎች የፋይናንሻል ዶክሜንት የሚከፈተው አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ይሆናል፡፡

  6. ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት የሚጠቀሙት ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው ዶክሜንት ላይ በመሆኑ ዋጋቸውን የሚሞሉት በዚሁ ሰነድ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡

  7. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10% በማስያዝ ባሸነፉበት በ7 ቀናት ውስጥ ውል ባይገቡ ለጨረታ ያስያዙት ለመንግስት ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡

  8. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስርዓት ባይገኙ የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

  9. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. ተጫራቾች የሚያቀርባቸውን የዕቃ ዓይነቶች ስም እና ሞዴል በዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

11. አንድ ተጫራች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

12. የርክክብ ቦታ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፡፡

ስለ ጨረታው የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- ስልክ ቁጥር 057 890 15 53/
057 775 20 36 ወይም 011 126 83 87

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)