Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-09-06

 

Tender Detail:

 




በ2009 በጀት ዓመት በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት ከሴፍቲኔት ካፒታል በጀት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የፋብሪካ ውጤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡

የተጫራቾች መመሪያ

  1. የታደሰ የዘርፉን ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ቲን ካርድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰነድ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡

  3. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦሪጅናሉን እና 2 የኦሪጅናል ኮፒ ለብቻው ቀን፣ ሙሉ ስም ከነአያት፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና የድርጅቱ ማህተም በትክክል ተደርጎ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡

  4. ፖስታው ከተከፈተ በኃላ ራስዎን ከጨረታ ማግለል አይችሉም፡፡

  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠው ቼክ / C.P.O/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  6. አጫራች መ/ቤት ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ይገባል፡፡

  7. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከ30ኛው ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡30 ሰዓት ኦፋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት አዲሱ ሕንፃ ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ሰንበት ከሆነ በቀጣዩ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾቹ በገዛ ፈቃድ በጨረታ ቦታ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡

  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኦፋ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ያሸነፈ ተጫራች በደብዳቤ ከተገለጸ በ3 ቀናት ውስጥ የውለታ ማስከበሪያ /Performance Bond / ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ/ ብቻ በመቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል፡፡

    1. 11.  የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ተጫራች እንደታወቀና ውል ከተፈራረመ በኋላ ለተሸናፊ ተጫራች ተመላሽ ይደረጋል፡፡

12. አሸናፊ ተጫራች ዕቃውን ኦፋ ወረዳ ፋይ ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ አድርሶ ያስረክባል፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የዋና ኃላፊ ቢሮ ስልክ ቁጥር 046 469 0141