Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

Dead Line: 2016-08-26

 

Tender Detail:

 



ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የ2009 ዓ.ም የሠራተኞች ደንብ ልብስና ጫማ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር አንድ መቶ ሀምሳ ብር /ብር 150.00/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡


  2. ዋጋቸውን በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡


  3. የጨረታ ሳጥን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ይከፈታል፡፡


  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፡-

4.1  በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ

4.2  ማንኛውንም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ

4.3  በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያስችል ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል

4.4  ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል

4.5  የጨረታ ማስከቢያ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የ2009 ዓ.ም የሠራተኞች የደንብ ልብስና ጫማ ማስረከቢያ ቦታ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡

  2. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን አሥር በመቶ (10%) የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
      
  3. ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀረቡበት ጊዜ የጫኝና አውራጅ ክፍያና ተያያዥ ወጪዎችን በማካተት ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

  5. ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማዕከላዊ ግዥ አዲስ አበባ አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ አጠገብ

ንዑስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 002 አንደኛ ፎቅ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ

(ሐረማያ) አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 15 (አዲስ አበባ)

ስልክ ቁጥር 0255530016 /0915747077

ፋክስ ቁጥር 02555303000  /354/325 አዲስ አበባ