Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ

Dead Line: 2016-09-03

 

Tender Detail:

 



በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/አርሲ ዞን የዶዶላ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በ2009 የበጀት ዓመት ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ

  1. የግንባታ /ሕንፃ/ መሳሪያዎች

  2. የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

  3. ብረት ብረት /የማኑፋክቸሪንግ/ ዕቃዎች

  4. የልብስ ስፌት ዕቃዎችና ጨርቃጨርቅ

  5. የሥልጠና የእጅ ማሳመሪያዎችን /hand tools/

  6. የተለያዩ ቋሚና አላቂ የስልጠና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ከሚጫረቱት ዕቃዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው እና የዕቃዎቹን ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡


  2. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡


  3. ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው እና የተ/እ/ታ/VAT/ ተጠቃሚ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡


  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /መቶ/ በመክፈል ከዶዶላ ቴ/ሙ/ት/እና ስልጠና ኮሌጅ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ /መግዛት ይችላሉ፡፡


  5. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በኮሌጅ በተዘጋጀው ሳጥን እንዲያስገቡ ይደረጋል፡፡ በዚሁ ዕለትም ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ /እሁድ/ ወይመ ብሔራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡


  6. ተጫራቾች /ወኪሎታቸው/ ባይገኙም በተገኙት ተወዳዳሪዎች ብቻ መ/ቤቱ ጨረታውን በተባለው ዕለት ለመክፈት ይገደዳል፡፡



  7. አሸናፊው ድርጅት ለግዢው የሚያቀርበው ደረሰኝ በሀገር ውስጥ ገቢና ጉምሩክ ባ/ሥ/መ/ቤት የፀደቀ መሆን አለበት፡፡


  8. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጻላቸው በ5 ቀን ጊዜ ውስጥ ከኮሌጁ ጋር ውል መፈራረም ይጠበቅባቸዋል፡፡


  9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ማጓጓዣ /ወጪ/ እስከ ኮሌጁ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡



  10.  ተጫራቾች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይገባቸውም፡፡


  11.   ተጫራቾች ከኮሌጁ በገዙት የጨረታ ሰነድ የአንዱ ዋጋ በሚለው ቦታ ላይ ያለምንም ስርዝ ድልዝ የሚሸጡበትን ዋጋ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተም በሰነዱና በፖስታው ላይ በማድረግ የጨረታው አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡


  12.   ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 ለተገለጹት የዕቃ ዘርፍ ለእያንዳንዳቸው ብር 3000 እና ከተራ ቁጥር 4 እስከ 6 2000 ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡


  13.   ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


  14.   ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ 09 10 10 99 40 /09 12 26 56 68 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡