Tenders

 

Type: Stationery

 

Organization: የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5

Dead Line: 2016-09-09

 

Tender Detail:

 



የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የተለያዩ፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች የደንብ ልብስ ቋሚ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ከላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለው እና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ገንዘብና ልማት ሚኒስቴር ለዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ በመስሪያ ቤታችን ስም በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 3/13/2008 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች እያንዳንዱ ዕቃ የሚሸጥበትን የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በወረዳ 5 የፋይናንስ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ መጫረት ይችላል፡፡    
  5. በጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ መጨረሻ ቀን ማለትም በ3/13/2008 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ግዥ /ንብ/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  6. ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘነበ ወርቅ ከታክሲ ማቆሚያ ከፍ ብሎ የሚገኘው የወረዳ 5 ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የፋ/ግዥ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ብር 50 በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                                               ስልክ ቁጥር፡- 0113696604/0911541619

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5

ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ

ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት