Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Dead Line: 2016-09-01

 

Tender Detail:

 

 

 

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የአንድራቻ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች ስራ አገልግሎት የሚውል፡-

  1. ጽህፈት መሳሪያዎችን
  2. ህንፃ መሳሪያዎችን
  3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን (ኮምፒውተሮችንና ላፕ ቶፕ)
  4. ሞተር ሳይክሎችን (150cc)
  5. ለሌሎች አላቂ ንብረቶችን በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉና ፍቃድ ያሳደሱ፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ቲን ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. የአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው፡፡
  5. እቃውን እስከ ወረዳ ማዕከል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 (ሦስት ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ ሆኖ ከዚህ በላይ ከ1-6 ተ.ቁ ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በነፃ እቃዎቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከወረዳው ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመውሰድ የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ በነጠላ ከነቫት ተሞልቶ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 7፡30 ሰዓት ታሽጎ  በዕለቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ በተገኙበት በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. በፖስታው ላይ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
  2. ያቀረቡት ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ መፃፍ አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- አድራሻችን ከዋና መድን አ/አ እስከ ጌጫ 711 ኪ/ሜ፣ ከጅማ እስከ ጌጫ 380 ኪ/ሜ፣ ከሚዛን እስከ ጌጫ 100 ኪ.ሜ ከቴፒ እስከ ጌጫ 52 ኪ.ሜ ሲሆን የሞባይል የስልክ ቁጥራችን 0943 21 39 84 እና 0949 56 00 80 መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት