Catagory Lists
Tenders
Type: Stationery
Organization: በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Dead Line: 2016-09-26
Tender Detail:
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2009 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ የሚያስፈልገውን ሎት አንድ የህትመት ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ንጉሴ ትሩፌ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ላይ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ዋናውንና ኮፒውን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ ተከታታይ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መስከረም 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ወይም መስከረም 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0112 73 25 91 /0112 73 20 02/0118 69 92 12 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ከመሳለሚያ ወደ ታይዋን በሚወስደው መንገድ ንጉሴ ቱሩፌ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ፡፡
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት