Catagory Lists
Tenders
Type: Multiple Items
Organization: በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት
Dead Line: 2016-09-21
Tender Detail:
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት በ2009 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶችና የስራ ሂደቶች የተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- የተለያዩ የህትመት ስራዎች
- ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች የሚያስፈልጉ ጎማ፣ ባትሪና የወንበር ልብሶችና ሌሎች
- ለተለያዩ ስራዎች የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎች ኪራይ
- የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና እና ሌሎች በግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፡፡
- የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጡ ማስረጃ /ታክስ ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 50.00 (ሐምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር በህግ ያስቀጣል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሂደት በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0118 60 71 05 ደውለው ያነጋግሩ፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ኮከብ ህንፃ 2ኛ ፎቅ፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት