Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Dead Line: 2016-09-26

 

Tender Detail:

 




የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ ስራ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎችንና የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ዝርዝሩ ከታች እንደተገለፀው ይሆናል፡፡

1ኛ. የቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎችን

2ኛ. የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን

3ኛ. ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 በተጠቀሰው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም የንግድ ዘርፍ ቀጥታ የሚገልጽ

4ኛ. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

5ኛ. የግብር መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

6ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፋቸውን እቃዎች ለማቅረብ ቅድሚያ ክፍያ ሳይጠይቁ መጪውን ሁሉ በራሳቸው ችሎ እንዲሁም በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡

7ኛ. ከላይ በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የንግድ ፈቃድ ቀጥታ ቧንቧና መገጣጠሚያ እና የኤሌክትሪክ እቃዎችን በማለት ቀጥታ የሚጋብዝ መሆን አለበት፡፡

8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለቧንቧና መገጣጠሚያ ዕቃዎች ብር 20000 /ሃያ ሺህ/ ለኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 8000 /ስምንት ሺህ ብር/ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በባንክ በተረጋገጠ CPO ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

9ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አርባ ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በመምጣት ብር የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

10ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበተ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ ኦርጂናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /በፖስታ/ በማሸግ ለስራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ በአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡

11ኛ. ተጫራቾች ተወዳድረው ማለፋቸው በድርጅቱ ሲነገራቸው ቀርበው ከድርጅቱ ጋር ውል በመግባት በ10 ቀን ውስጥ ዕቃውን ማስገባት አለባቸው፡፡

12ኛ. ማንም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡

13ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0468810369/0468812049/ መደወል ይቻላል፡፡

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጋሞ ጎፋ ዞን የአርባ ምንጭ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

የጨረታ ማስታወቂያ 10/09