Tenders

 

Type: Services

 

Organization: በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንናዱር እንስሳት ድርጅት

Dead Line: 2016-09-21

 

Tender Detail:

 



በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንናዱር እንስሳት ድርጅት ቀጥሎ የተጠቀሱትን የዱር እንስሰሳት የቁጥጥር አደን ቀበሌ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለ5 /አምስት/ ዓመታት በኮንሴሽን መስጠት ይፈልጋል፡፡

  1. የታደሰ የዱር እንስሳት አሳዳኝነት ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እያንዳንዱ ተጫራች ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ/ አጠገብ በሚገኝ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ሰነድ በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. ይህ የዱር እንስሳት የቁጥጥር አደን ቦታ የሚገኘው እሉ አባቦራ ዞን በቻዋቃ፣ መኮ፣ ጊምቢ እና ሐሮ ወረዳዎች ልዩ ስሙ ሐሮ አባዲኮ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቦታ በአሁን ጊዜ የሚተዳደረው ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በእሱ አባቦራ ቅርንጫፍ ነው፡፡ የቦታው ስፋት 248 km2 የቆዳ ስፋት ያለው ነው፡፡
  3. ይህ የዱር እንስሳት የቁጥጥር አደን ቦታ የሚገኘው አርሲ ዞን መስተዳደር ጉና ቾሌና አንንጣ ወረዳዎች ልዩ ስሙ ውርጋን ቡላ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቦታ በአሁኑ ጊዜ የሚተዳደረው ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት አርሲ ቅርንጫፍ ነው፡፡ የቦታውም ስፋት 18km2 የቆዳ ስፋት ያለው ነው፡፡

በመሆኑም፡-

  1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ/ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት እና የሚዘጋበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
  2. ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ያቀረቡትን የጠቅላላውን ዋጋ 10% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0111240249 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት