Tenders

 

Type: Services

 

Organization: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-10-25

 

Tender Detail:

 



የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር የሥራ ሂደት ከዚህ በታች
የተጠቀሰውን በዲጂታል ዲስኘሌይ (LED) ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ
በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ በሆነ ድርጅት ለማሰራትይፈልጋል::
በዲጂታል ዲስኘሌይ (LED) ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ግዥ ግልፅ
ጨረታ ቁጥር 17/2016/17
 
 

የአገልግሎቱ ዓይነት:-በዲጂታል ዲስኘሌይ
(LED) ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ

ተፈለገው ብዛት:-52

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
በሲፒኦ ወይንም ቅድመ ሁኔታ
ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና-10,000.00

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ፤

1.የታደሰንግድ ፈቃዳቸውን፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር
ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ውስጥ የተመዘገቡበትን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ
የተመዘገቡበትን ማስረጃ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ
የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን
ከሐሙስ መስከረም 19ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት
ከጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 ቫቲካን ኤምባሲ
አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር
ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ::

2.ተጫራቾችስለጨረታው መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-
3722858/011-8964493 በፋክስ ቁጥር 011-3722889 ዳይሬክተር
ዕቃ አቅርቦት እና አስተዳደር መጠየቅ ይችላሉ::


3.ተጫራቾችየጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት ትክክለኛ የሆነ የቀጥታ
መስመር ስልክ ቁጥር፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፤ የኢሜል አድራሻ
እና የፋክስ ቁጥር ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።ሆኖም ግን ማንኛውም
ተጫራች ትክክለኛ አድራሻ ሳይሰጥ ቢቀር ወይም በማንኛውም
ምክንያት የሰጠው አድራሻ ሳይሰራ ቀርቶ በባንኩ የተላከ ማንኛውም
ዓይነት መረጃ ባይደርሰው ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።


4.ተጫራቾችለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በሲፒኦ ሰነዱ ውስጥ
በተጠየቀው መልኩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::


5.በዲጂታልዲስ ኘሌይ (LED) ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ሥራ
ጨረታ ጥቅምት 15ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከላይ
በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ቦታ ይዘጋል:: ተጫራቾች በዲጂታል
ዲስኘሌይ (LED) ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ሥራ ጨረታ እስከ
ጥቅምት 15ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እያስመዘገቡ
ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::


6.ተጫራቾችበጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው የፍላጐት መግለጫ
ዝርዝር መሠረት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::


7.በዲጂታልዲስኘሌይ (LED) ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ሥራ
ጨረታ ጥቅምት 15ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ
በተራ ቁጥር 1 በተጠቀሰው ቦታ ለመገኘት ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች
ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል::


8.ባንኩየተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ
መብቱ የተጠበቀ ነው::