Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Dead Line: 2016-10-24

 

Tender Detail:

 





የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቡታጂራ ቅርንጫፍ ለሚገነባው ህንፃ (G+M+4) በባንኩ የተዘጋጀዉን ስ
ታንዳርድ ዲዛይን ከሳይቱ ጋር የማጣጣም ስራ እንዲሁም የግንባታ ቁጥጥር /Supervision/ እና
ኮንትራት አስተዳደር ስራ ለማሰራት ደረጃቸው Category III እና ከዛ በላይ የሆኑ ፍቃዳቸውን ያ
ሳደሱ፣ ከመሠረተ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ የዘመኑን ግብር የከፈ
ሉ አርክቴክቶችና መሀንዲሶች አማካሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::
በመሆኑም፦

1.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የአማካሪ ድርጅቶችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይ
መለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተ
ዳደር በሚገኘበት ቫቲካን ኤምባሲ ወረድ ብሎ በቀድሞ ሚድሮክ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥ
ር 202 ህንፃ ግንባታ ክፍል ከመስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ::

2.ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒካል ሰነድ ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የዋጋ ሰነድ
ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ (በማሽን ኮፒ) ሰነዶችን ለየብቻ የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ በሰም
በታሸገ ኢንቭሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ
ጥቅምት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በፊት በማስመዝገብ ማስገባት አለባቸው።


3.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ( BID BOND) ብር10,000.00 / አስር ሺህ ብር/ በ
ባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (un-
conditional Bank guarantee) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::

4.ተጫራቾች ጨረታውን ሲገዙ የንግድ ፍቃድ፣የሥራ ፍቃድ፣የታክስ ከፋይነት ማስረጃ (ቲን
ሰርተፍኬት) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውና የታደሰ ታክስ
ክሊራንስ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብአለባቸው::


5.ጨረታው ጥቅምት 14ቀን 2009 ዓ.ም .ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪ
ሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲሊቲዎች አስተዳደር ህንፃ በሚገኘው የመ
ሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::


6.ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113 - 691545/722872/69