Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

Dead Line: 2016-10-11

 

Tender Detail:

 

 



በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች (ናሙና) መቅረብ አለበት፡፡

ሎት 2 አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች (ናሙና) መቅረብ አለበት፡፡

ሎት 3 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ (ናሙና) መቅረብ አለበት፡፡

ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 5 የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች

ሎት 6 የህንፃ መሳሪያዎች ግዥ

ሎት 7 የችግኝ ዘር፣ ሰምና የንብ መንጋ

ሎት 8 የተለያዩ የመኪና እቃዎች ጎማ፣ ባትሪዎችና ሌሎችም

ሎት 9 ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ኮፒ ማሽን፣ የስልክ የውስጥ መስመርና ሌሎችም ጥገና አገልግሎት ግዥ

ሎት 10 የሆቴል አገልግሎት ግዥ

ሎት 11 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ

ሎት 12 የፍሳሽ ቆሻሽ ማስመጠጥ አገልግሎት ግዥ

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ለመካፈል የዘመኑ የታደሰና አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ከብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ ባለው ግዢ ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡   
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡  
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናተ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት የሚከፈተው የዕቃ ግዥዎች ከሎት፡- 1 እስከ 8 ያሉት ሎቶች ሲሆኑ ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓተ የሚከፈቱት ሎቶች ደግሞ የአገልግሎት ግዥዎች ከሌት 9 እስከ 12 ያሉት የአገልግሎት ግዥዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ /የመዝጊያውም ሆነ የመክፈቻው ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከመ/ቤቱ ከፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደትና ግዥና ንብረት ደ.ስ. ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 እና 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ሲ.ኤም.ሲ በሚወስደው መንገድ ጉርድ ሾላ አለፍ ብሎ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ሉሲ አካዳሚ ት/ቤት አጠገብ፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 011 667 51 14

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን