Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም

Dead Line: 2016-10-25

 

Tender Detail:

 



የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም
ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የሚውል ጤፍ፣ የቆሎ፣ ድፍን ባቄላ፣ የማገዶ እንጨት እና ማጣፈጫዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት በዘርፉ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች፡-

1ኛ. የታደሰ ንግር ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡

2ኛ.በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የእህል ዓይነቶች ለ 6 ወራት  በሚፈለገው  መጠን ጥራትና ደረጃ በጠበቀ መልኩ  በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር  ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

3ኛ. አሸናፊ ድርጅት ጤፋን በተቋሙ ግቢ ውስጥ አምጥቶ በማስበጠር 100ኪ.ግ መዝኖ ማስረከብ የሚችል፣

4ኛ.ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 የተገለጹትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው  ዋጋ ማቅረቢያ ጋር ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5ኛ.ማንኛውም  ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ቢድ ቦንድ ብር 60,000/ስልሳ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6ኛ.የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ ጥቅምት 15/02/2009ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7ኛ. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ጥቅምት 15/02/09 ዓ.ም በ6፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

8ኛ.ተጫራቾች ከሐዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 50 ብር መግዛት ይኖርባቸዋል፣


ማሳሰቢያ

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የማጣፈጫና የማገዶ እንጨት ጨረታ የሚከፈተው ሐሙስ 17/02/09 ዓ.ም በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ስልክ ቁጥር 0462205825 ፖስታ 1217