Tenders

 

Type: Construction

 

Organization: የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ከዓለም አቀፍ ልማት ምህበር (IDA)

Dead Line: 2016-11-04

 

Tender Detail:

 



1. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ከዓለም አቀፍ ልማት ምህበር (IDA) ያገኘውን የፕሮጀክት ገንዘብ

(Performance Grant ) ለከተሞች ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ( ULGDP-II ) ይውላል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፈሉ በሕዝብ ተሳትፎ ለተመረጠ የምርት ማሳያ ማዕከል ሼድ ግንባታ (Display center shade construcion) ስራ ይውላል፡፡


2. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስተዳደር ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የምርት ማሳያ ማዕከል ሼር ግንባታ(Display center shade construcion) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡


3. በዘመኑ የተሰደሰ ሕጋዊ የጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ GC-8 እና በላይ እና የህንፃ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ GC -7 እና በላይ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት መውዳደር ይችላሉ፡፡


4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡


5. የግብር ከፋይ መለያ መለያ ቁጥር( TIN ) ያላቸው፡፡


6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡


7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.3 እስከ 6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡


8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 25/2/2009 ዓ.ም ከግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይቻላል፡፡


9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት 2% ተጫራቹ ካቀረበው ጠቅላላ የተስተካከለ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡


10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የደሴ ከተማ አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 28/2/2009 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡


11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 9 በ28/2/2009 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ሲከፈት ከላይ ከተ.ቁ.3 እስከ 6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም

በስልክ ቁጥር 033 111 6130 ወይም 033 112 4913 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡