Catagory Lists
Tenders
Type: Autos
Organization: የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ፍትህ ቢሮ
Dead Line: 2016-03-05
Tender Detail:
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ፍትህ ቢሮ የሚገለገልባቸው መኪናዎች የአንድ ዓመት የሚቆይ በኮንትራት ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሣተፉ ይጋብዛል፡፡
-
-
- በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ፋቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN number) ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከትራንስፖርት ቢሮ ወይም ከክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ የደረጃ 3 ወይም ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ በሚያቀርብ ዋጋ ላይ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO)ጨረታው በመክፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመሥሪያ ቤቱ ግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) በመጨመር የቴክኒክና ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በተለያዩ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/በማሸግ ዘውትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ፋትህ ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት/16ኛው ቀን/ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡05 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና አገልግሎት መስጫ ቦታ ያላቸው በሆኑን ለጨረታው ኮሚቴ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሠሪው መ/ቤት አገልግሎት ማግኘት የሚፈለገው በሃዋሳ ከተማ ነው፡፡
- ጨረታው ውስጥ እስከሚገለጽ ጊዜ ድረስ የፀና ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ፋቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0462207327 ደውለው ይጠይቁ፡፡