Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ

Dead Line: 2016-11-12

 

Tender Detail:

 

 

 

የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2009 በጀት ዓመት ለኮሌጅ ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ፡-

  1. የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች

  2. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች

  3. ብረት ብረቶችና የብረታ ብረት ስራ  መሳሪያዎች

  4. ላፕቶፕ፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮች

  5. የአይቲ ስልጠና ቁሳቁሶች

  6. የቅየሳ መሳሪያዎች

  7. የአውቶሞቲቭ ስልጠና መሳሪያዎች

  8. ሞተር  ሳይክሎችን

  9. የኤሌክትሪክሲቲ ቁሳቁሶችን

  10. የእንጨት ስራ ማሽኖችና መሳሪያዎች

  11. የቢሮ ወንበሮችና ጠረጴዛዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ በሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የምግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ሸካ ዞን ማሻ ከተማ በሚገኘው የማሻ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 1 ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም  በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት ፈርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት ተከታታይ የመንግስት ስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡

  5. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡

  6. 16ኛው ቀን የመንግስት ስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ  ይከፈታል፡፡

  7. የጨረታው አሸናፊ የሆነው  አቅራቢ  በራሱ ወጪ አቃውን አጓጉዞ ሸካ ዞን ማሻ ከተማ እስከ ኮሌጁ ድረስ በማምጣት ያስረክባሉ፡፡

  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ  ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  9. አንዳንድ ማሽኖችና መሳሪያ አቅራቢዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  10. የጨረታ አሸናፊዎች ከተለዩ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው 10%ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ  የተጠበቀ ነው፡፡

  12. ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 558 05 38/0912 44 62 41 መደወል ይቻላል፡፡