Tenders

 

Type: Autos

 

Organization: ቡና ኢንሹራንስ አማ

Dead Line: 2016-11-04

 

Tender Detail:

 




ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችንባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹንና የተሽከርካሪ አካላትን መግዛት ለሚፈልጉ አራት ኪሎ ደብር ሕንፃ 3ኛፎቅ በሚገኘው የኩባንያችን ዋና መ/ቤት ወይም የኩባንያችን ሪከቨሪ ግቢ በመገኘት የተዘጋጀውንሰነድ ብር 30.00 በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የሚገዙበት ዋጋ በተዘጋጀውየዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 11ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ::

 
ተጫራቾች ንብረቾችን እና ተሽከርካሪዎችን ቃሊት ቆርኪ ፋብሪካ ወደ ቁስቋም ማሪያምበሚወስደው መንገድ የአስፋልቱ መጨረሻ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ ከጥቅምት 14 ቀን 2009 እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ::
 
ጨረታው ቅዳሜ ጥቅምት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 4 ሰዓት በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤትተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
 
ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም::

 
ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በቡና ኢንሹራንስአ.ማ ወይም Bunna Insurance S.C ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 200 (ሁለት መቶ ብር)ማነስ የለበትም::
 
ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሸከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሽከርካሪዎች እና የተሽከረካሪ አካላትከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፈናል:: በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው
በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል::

 
የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስትበመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ::

 
አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለው 10 የሥራ ቀን ውስጥ ክፍያፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ
ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል::

 
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግየተጠበቀ ነው::

ቡና ኢንሹራንስ አማ
አራት ኪሎ ዳብር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
(011-1-262861/ 1-26314