Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የምሥራቅ አካባቢ ፅ/ቤት

Dead Line: 2016-11-18

 

Tender Detail:

 

 

በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የምሥራቅ አካባቢ ፅ/ቤት (ሐረር) Family Guidance Association of Ethiopia- Eastern area Office (Harar) የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ ፕሪንተሮችን፣ እሰታብላይዘሮችን፤ ፎቶኮፒ ማሽኖችን፤ ፍሪጆችን፣ ወንበሮችን፣ ጠረጴዛዎችን፣ ፋይል ካቢኔቶችን፤ ማይክሮስኮፖችን፤ የክብደት ሚዛኖችን፤ ሳይክሎችን፤ ዲቪዲዎች፤ የጠረጴዛ ቴኒችን፤ የውኃ ታንከር፤ የመኪና ጎማዎችን፤ ሞንታርቦ እስፒከሮችን፣ ብስክሌቶችን፤ ቴፕሪከርደሮችና የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ሕጋዊ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል::
 
የጨረታውን ዶክመንት ስለመግዛት፡- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 ብቻ በመክፈል ከሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የምሥራቅ አ/ፅ/ቤት (ሐረር) ቢሮ ቁጥር 1 እና በአዲስ አባባ በዋናው መ/ቤት (ሪቼ አካባቢ) ቢሮ ቁጥር 303 ቀርበው መግዛት ይችላሉ:: ተጫራቾች የሚከተሉትንመስፈርቶችና ሁኔታዎች መሟላትና ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡
 

1.የዓመቱን የመንግስት ግብር የገበረ እና በዘርፉ ላይ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው ፣


2.ተጫራቾች ይህ መስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት የሚሸጡትን ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎችን፣ ኮምፒውተሮችን፣ ፕሪንተሮችን፣ እሰታብላይዘሮችን፤ ፎቶኮፒ ማሽኖችን፤ ፍሪጆችን፣ወንበሮችን፣ ጠረጴዛዎችን፣ ፋይል ካቢኔቶችን፤ ማይክሮስኮፖችን፤ የክብደት ሚዛኖችን፤ ሳይክሎችን፤ ዲቪዲ ማጫወቻዎችን፤ ሞንታርቦ እስፒከሮችን ቴፕሪከርደሮችንና የተለያዩ ንብረቶችን በሐረር ከተማ ቀበሌ 07 እስታዲየም ጀርባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የምሥራቅ አካባቢ ፅ/ቤት ግምጃ ቤት ቀርበው ከሀሙስ ህዳር 01 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ረቡዕ ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ወይም መጎብኘት ይችላሉ::
 
3.ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት ንብረት የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ዶክመንት ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የድጋሚ ማስታወቂያው ለመጀመሪያ ጊዜ በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ከወጣበት ከእሑድ ጥቅምት 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 14 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ አድራሻ ማለትም በሐረር ከተማ ቀበሌ 07 እስታዲየም ጀርባ በሚገኘው በሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የምሥራቅ አካባቢ ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቢሮ ቅፅር ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::

 
4.ተጫራቾች ለሚጫረቱበትየተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ /Family Guidance Association of Ethiopia Eastern Branch Office/ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ፖስታ ውስጥ አብሮ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል::


5.ጨረታው ረቡዕ ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ሰዓት በሐረር ከተማ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው::


በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድቦንድ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል:: የጨረታ አሸናፊዎች የገዙአቸውን ንብረቶች የማጓጓዣ ወጪዎችንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናሉ::

 
6.በጨረታው ለሚሸነፉትያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ የጨረታ አሸናፊው ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመየሚመለስላቸው ይሆናል::

 
7.ድርጅቱ ጨረታውንበከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው::


አድራሻ: በኢትዮጰያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የምሥራቅ አካባቢ ፅ/ቤት
ስልክ : 0256667237/0256667238/0114672300
ፖ.ሳ.ቁ 981, ሐረር, ኢትዮጵያ.