Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: በድሬ ዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ፅ/ቤት

Dead Line: 2016-11-25

 

Tender Detail:

 በድሬ ዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ፅ/
ቤት በ2009 በጀት ዓመት በተያዘ የአስተዳደሩ በጀት ለመስተዳድሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቢሮዎችና ፅ/ቤቶች የሚያስፈልጉትን ኤሌክትሮኒክሶች፤ ፈርኒቸሮች ፤ የተለያዩ ቶነሮችና ወረቀቶችን በማእቀፍ ግልጽ ጨረታ እንዲሁም ሌሎች ግዥዎችን ማለትም የተለያዩ ህትመቶችን፤ተሸከርካሪዎች ፤ የኢንጅነሪንግ ማቴሪያሎችን እና ለመስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ ቤትና ለቡዙሀን
መገናኛ ኤሌክትሮኒክሶችን በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1.ዘርፉ የንግድ ስራ የተሠማሩና ሕጋዊ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፣

2.ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣


3.ዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣


4.ጫራች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሠነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣


5.ጫራቶች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ህዳር 12/2009 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 102 ቀርበው በመውሰድ አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በመግለጽ ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገውማስገባት ይችላሉ፣

6.ጨረታ ሳጥኑ ቶነር እና ወረቀት ህዳር 14 ቀን 2009ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ በግልጽ ይከፈታል ፤ ፈርኒቸር ህዳር 15 ቀን 2009ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ በግልጽ ይከፈታል።

ተሸከርካሪእና ኢንጂነሪንግ ማቴሪያል ህዳር 15 ቀን 2009 ዓ.ም ከሠአት በኋላ 9፡00 ታሽጎበዚሁ እለት ከሠአት 9፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በጽ/ ቤቱ በግልጽ ይከፈታል።
ኤሌክትሮኒክስ ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ
በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ
 በግልጽ ይከፈታል ።
ህትመት ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም ከሠአት በኋላ 9፡00 ታሽጎ በዚሁ 
እለት ከሠአት 9፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ በግልጽ ይከፈታል።

7.ጫራቶች ብር 57,000 ለቶነር፤ 50,000 ለወረቀት፤ 17,000 ለፈርኒቸር፤17,000 ለኤሌክትሮኒክስ ፤ 25,000 ሀርድ ቶፕ ደብል ጋቢና ፒክ አፕ ፤ 15,000 ለሞተር ባይስክል፤ 10,000 ለሀይሩፍ ሚኒባስ ፤ 3000 ለህትመት እና 3000 ለኢንጀነሪንግ ማቴሪያል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

8.ስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.ጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡-

በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግለሎት
የስልክ ቁጥር 0251-11-54-02
ፋክስ ቁጥር 0254-11-01-79