Tenders

 

Type: Furniture

 

Organization: ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

Dead Line: 2016-11-15

 

Tender Detail:

 

 




የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ልዩ ልዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የሚሸጡትን ዕቃዎች ቃሊቲ በሚገኘው የመቤ/ቱ መጋዘን በአካል በመገኘት ዘውትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9፡00  ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋናው መ/ቤት 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 104 ብር 30.00 ከፍለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራቾች አሸናፊ ከሆነበት ቀን ጅምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጥቅል ዋጋ መክፈልና ዕቃውንም ማንሳት አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫራቱበትን ዕቃዎች ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ህዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ መንገድ ባለሥልጣን ዋናው መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አጠቃላይ የጨረታ መነሻ ዋጋ አስር መቶ (10%)  በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ያቀረበ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. ተጫራቸች በአንድ (በሌላ ተጫራች) ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በመሥሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  9. መሥሪያ ቤቱ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ሽያጭ በተመለከተ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

      የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

        የዕቃ ግዥና አቅርቦት ቡድን

         የፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770

ስልክ ቁጥር፡- 011 553 04 23 ወይም 011  551  71 70 

          የውስጥ መስመር 174 ወይም 164

        ፋክስ ቁጥር፡- 011  550  77 88 

                አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

             ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን