Tenders

 

Type: Multiple Items

 

Organization: የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

Dead Line: 2016-11-27

 

Tender Detail:

 




የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለራስ ሃይሉ መዋኛ ገንዳ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Spectatore Plastic seat የአቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
 
ስለሆነም፡-

1.ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

 
2.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት።

 
3.ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋናው መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ።


4.ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (Product Quality Certificate) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 
5.ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል።

 
6.በተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ህዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

 
7.ጨረታው ህዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

8.ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


አድራሻ፡-የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ114-4ዐ-34-34/33
ማዞሪያ ዐ114-42-22-70/71/72